CO2 የመፍላት ዘዴ የቡና ጥራትን ያሻሽላል
Back

CO2 የመፍላት ዘዴ የቡና ጥራትን ያሻሽላል

ECTA
5 min read

በቅርቡ በኮሎምቢያ የተካሄደ አዲስ ጥናት እንደጠቆመው፤ የታሸገ ኮንቴይነር እና መጠነኛ የካርቦን ዳይኦክሳይድ (CO2) ጋዝ አጠቃቀም ተራ የሆኑ “ናቹራል” ቡናዎችን ወደ ከፍተኛ የልዩ (Specialty) ቡና ሊያሸጋግራቸው ይችላል።

ጥናቱ ክፍት በሆነ አየር እና በካርቦን ዳይኦክሳይድ የታገዘ (Closed Fermentation) ዘዴዎችን በማነፃፀር በኮሎምቢያ የቴክኖሎጂ ተቋም (SENA) እና በቫሌ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተከናወነ ነው። ተመራማሪዎቹ ከአንድ ማሳ የተለቀሙ የቡና ፍሬዎችን ከመድረቃቸው በፊት አምስት አይነት አፕሮች በመጠቀም Ferment በማድረግ፤ ቡናው ደርቆና ተቆልቶ በዓለም አቀፉ የልዩ ቡና ማህበር (SCA) ከ100 ነጥብ መለኪያ ተመዝኗል።

በዚህም ለ24 ሰዓታት በካርቦን ዳይኦክሳይድ በታፈነ ስፍራ የቆየው ቡና 86.90 አማካኝ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ ሲወጣ፤ ምንም አይነት ሂደት ያልተደረገበት ቡና ደግሞ 82.15 ነጥብ ብቻ አግኝቷል።

በታህሳስ 2025 በታዋቂው Scientific World Journal ላይ የታተመው ይህ ጥናት፤ በልምድና በጥቃቅን ሙከራዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ ለሚሰራው የልዩ ቡና ገበያ፣ በሳይንሳዊ መንገድ የተረጋገጠ እና በሰፊው ሊተገበር የሚችል አዲስ አቅጣጫ እንደሚያመላክት ተገልጿል።

ተመራማሪዎቹ እንዲህ ብለዋል፦

“ምንም እንኳ በቡና Fermentation ሂደት ላይ በርካታ ምርምሮች ቢደረጉም፣ አብዛኞቹ በላቦራቶሪ ቁጥጥር ስር ወይም በታጠበ ቡና (Wet processing) ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው፤ በፀሐይ በሚደርቅ (Natural) ቡና ላይ ያላቸው ተፈጻሚነት ውስን ነበር። በተለይም በካርቦን ዳይኦክሳይድ የታገዘ የFermentation ዘዴ በተፈጥሯዊ የቡና አዘገጃጀትና በኬሚካላዊ ይዘት ላይ ያለውን ተፅዕኖ በተጨባጭ የምርት ቦታዎች ላይ የሚያሳይ ሳይንሳዊ መረጃ እጥረት ነበረው።”

ይህ አዲስ ግኝት ለቡና አምራቾች ጥራትን ለማሻሻል ቀላልና ውጤታማ መንገድ ይጠቁማል ይለናል አዲሱ ጥናት።

CO2 Fermentation Boosts Natural-Process Coffee Scores in Colombian Trial

Daily Coffee News March 17, 2026

https://dailycoffeenews.com/.../co2-fermentation.../...

Gallery

Gallery image 1

Tags

#ECTA#coffee