''ቡና የገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ሀገራችንን ለአለም ክፍ ያደረገ ብርቅዬ ሀብታችን ነው:-'' ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
Back

''ቡና የገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ሀገራችንን ለአለም ክፍ ያደረገ ብርቅዬ ሀብታችን ነው:-'' ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

ECTA
5 min read

''ቡና የገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ሀገራችንን ለአለም ክፍ ያደረገ ብርቅዬ ሀብታችን ነው:-'' ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

ቡና የገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ሀገራችን ስም ለአለም ክፍ ያደረገ ብርቅዬ ሀብታችን ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቡና አብቃይ የሆኑ በተለያዩ ወረዳዎች የቡና የምርት አሰባሰብ ሂደት የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው።

በባህላችንም ለቡና የሚሰጠው ቦታ ከፍተኛ ነው ያሉት ርዐሰ መስተዳድሩ ከዛም ባለፈ ክልላችን ብሎም ሀገራችን ለአለም በከፍተኛ ደረጃ የዉጭ ምንዛሬ እንድታገኝ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

ቡናን የምያምርቱ አርሶ አደሮች እና በቡና ንግድ የተሰማሩትን ሁሉ ለአለም መድረክ ያስተዋወቀና እያስተዋወቀ ያለ ብዙዎችን ሕይወት የቀየረ ባለውለታችን ነው ብለዋል።

ምርቱን ማሳደግና ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለአለም ገበያ ለማቅረብ ቡናን ከማሳ ጀምሮ ገበያ እስከቀርብ አስፈላጊውን እንክብካቤ ልናደርገው ይገባል በማለት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::

የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው በክልሉ በቡና ሽፋን 171 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መድረሱን ገልጸዋል ።

የዘንድሮ የኤሼት ቡና ከታቀደው ውስጥ ለማዕከላዊ ገበያ 40ሺህ ቶን ለማቅረብ መታቀዱን አቶ መምሩ ሞኬ ገልጸዋል ።

በክልሉ ሕግ ወጥ የቡና ግብይት ለመከላከል ግብረ ኃይል በማቋቋም ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል::

እርሻና ተፈ/ሀብት ልማት ቢሮ የህዝብ ግኝኑነት

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#ecta#coffee