በሸማቾች  መብት  ጥበቃ ስራዎች  ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና  እየተሰጠ ነው
Back

በሸማቾች መብት ጥበቃ ስራዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው

Motri
5 min read

በሸማቾች መብት ጥበቃ ስራዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው

=======================

አዲስ አበባ ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሸማቾች መብት ጥበቃና ግንዛቤ ዴስክ በክልልና እና ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ በሸማቾች መብት ጥበቃ ላይ ለሚሰሩ አመራሮች እና ለሸማቾች መብት ጥበቃ ሲቪክ ማህበራት አመራሮች በሸማቾች መብት ጥበቃ ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና በአዲስ አበባ በጥራት መንደር እየሰጠ ይገኛል።

የስልጠናው ዓላማ የሸማቾች መብት ጥበቃ ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ የሸማች ጥበቃ ስራዎች በዕውቀት እንዲመራ ለማስቻል ነው።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሸማቾች መብት ጥበቃና ግንዛቤ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይፉ አየለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ላይ በተለያዪ ጊዜያት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠቱን በመግለጽ በተፈጠሩ ግንዛቤዎችም በርካታ ለውጦች ተገኝተዋል ብለዋል።

የተደራጁ የሸማች መብት ጥበቃ ማህበራት በአህጉርና በአለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመርና ከንግድ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በሸማቹ ላይ ለሚደርሰው ችግር ሸማችን ወክለው እንዲሞግቱ የተቋቋመ አደረጃጀት መሆኑን የጠቆሙት የዴስክ ኃላፊው በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሸማቹ ህብረተሰብ ለከፈለው ገንዘብ ተመጣጣኝና ጥራት ያለው ምርት እንዲያገኝ የማህበራቱ ሚና የማይተካ መሆኑን ገልጸዋል።

የስልጠና ተሳታፊዎችም ያገኙትን ግንዛቤ በየደረጃው ካሉ ንግድ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በሸማቹ ላይ የሚደርሱ የጤንነትና የኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ለመከላከል ግንዛቤ እንዲፈጥሩ አቶ ሰይፉ አሳስበዋል፡፡

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#Motri#coffee