በንግድ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ለነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሠራተኞች በንግድ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ አጠቃላይ የሪፎርሙን ይዘት በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡
ለአጠቃላይ ሰራተኛው በተዘጋጀው ስልጠና መድረክ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ተገኝተው ሪፎርሙን የተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸው ይህ ሪፎርም ሠራተኛን ለመቀነስ ታስቦ የመጣ ሳይሆን ብቃት ያለውና ብቁ የሆነ አገልግሎት ሰጪ ሲቪል ሰርቫንት ለማፍራት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አቶ ሲሳይ ባይከዳኝ የሪፎርሙን አተገባበር አስመልክተው ስልጠናና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡




