በምርት ዘመኑ  ከ11ሺ ቶን በላይ ቡና  ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ  እየሰራ መሆኑን የሸኮ ወረዳ  ግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ፅ/ቤት አስታወቀ።
Back

በምርት ዘመኑ ከ11ሺ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የሸኮ ወረዳ ግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ፅ/ቤት አስታወቀ።

ECTA
5 min read

ሚዛን አማን- ጥቅምት23/2018   

በቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት  የቡና ፣ ሻይና  ቅመማ ቅመም እና ምርት ዝግጅት አስተባባሪ አቶ አንለይ እንየው እንዳሉት በተያዘው  የምርት ዘመን ከ11ሺ ቶን በላይ  የታጠበና  ያልታጠበ ቡና  ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ  በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም 19 የቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመዋል። በምርት ዘመኑ የታጠበ 1ሺ ቶን  እና ያልታጠበ ከ10 ሺ ቶን  በድምሩ 11ሺ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

በምርት አሰባሰብና ግብይት ወቅት የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን በቅንጅት በመፍታት ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ከቡና ጥራትና ቁጥጥር ግብረ ሀይል ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በወረዳው እየለማ ካለው  33ሺ 4 መቶ ሄክታር በላይ ቡና ውስጥ 24ሺ ሄክታር በላይ ማሳ ምርት በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን አቶ  አንለይ ገልጸዋል።(ቤሸቴ)

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#sidama#ecta#coffee