Adwa Victory Celebrated
Back

Adwa Victory Celebrated

Motri
5 min read

ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብህ አድማስ!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 130ኛውን የዓድዋ የድል በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብህ አድማስ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት አክብረዋል።

በበዓሉ አከባበር ላይ የውይይት መነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ፣ የዓድዋ ድል የጥንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በአንድነትና በጀግንነት ያስመዘገቡት ታላቅ የታሪክ አሻራ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዝናቡ በዝርዝር እንዳብራሩት፣ ይህ ድል ኢትዮጵያውያን በጋራ ከቆሙ የማይበገሩ መሆናቸውን ለዓለም ያስመሰከሩበት ክስተት ነው።

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና ቆራጥነት አይበገሬነቷን በዓለም አደባባይ ያስመሰከረችበት የጥቁሮች ብሎም የአፍሪካ ድል ነው፡፡

ኃላፊው አክለውም፣ የአሁኑ ትውልድ ከዚህ ታላቅ ድል ሊማረው የሚገባው ዋነኛ ቁምነገር በጋራ ጥረት ሀገራዊ ራእይን ማሳካት መሆኑን ጠቁመዋል።

“ከአሁኑ ትውልድ የሚጠበቀው የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በአንክሮ ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን የጀመረቻቸውን የልማትና የብልጽግና ስራዎች ለማሳካት በተሰማራንባቸው የሙያ መስኮች ሁሉ በተለይም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ዘርፍ በታማኝነትና በትጋት መስራት ነው” ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችም በበኩላቸው፣ የዓድዋ ድል ለስራ ተነሳሽነት ትልቅ ጉልበት እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው፣ የአባቶቻቸውን ጀግንነት በልማት ለመድገም ቃል ገብተዋል። በተለይም የንግድ ስርዓቱን ለማዘመንና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9
Gallery image 10

Tags

#Motri#coffee