5.1 ቢሊዮን ዶላር ከውጪ ንግድ ገቢ
Back

5.1 ቢሊዮን ዶላር ከውጪ ንግድ ገቢ

Motri
5 min read

ከወጪ ንግድ ገቢ 5.1 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ: ጥር 26/ 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ10ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

በስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከወጪ ንግድ ገቢ 5.1 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱንና ይህም የእቅዱን 120% መፈፀሙን ገልፀዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከወጪ ንግድ ገቢ ከ2017 በጀት ዓመት በፊት በነበሩት ዓመታት በዚህ ደረጃ ስኬት ማምጣት ቀርቶ አቅዳ እንደማታውቅ አንስተዋል።

Gallery

Gallery image 1

Tags

#Motri#coffee